=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
እንግዲያውስ የሚከተሉትን ነገሮች የሂወትህ መርህ አድርግ/ጊ:-
Δ የተመጣጠነ ምግብ ተመገብ
- ቪታሚን
- ፖሮቲን
- ካርቦሃይድሬት
- ሊፒድ
Δ አካልህን ልብሶችህን የመመገቢያ እቃዎችህን ቤት ደጅህን ከቆሻሻ አፅዳ ከቆሻሻ የፀዱ አድርግ
Δ የአካል እንቅስቃሴ(ስፖርት) ስራ
Δ ንዴት ፍርሃትና ጭንቀትን አስወግድ
Δ ስራዎችህን በእቅድ ስራ
Δ ጤናማ የሆነ ማህበራዊ ሂወትን መስርት
Δ ጤና ጋር ተያያዥነት ያላቸው መጽሐፎችን አንበብ የቴሎቪዥን ፕሮግራሞችንም ተከታተል
Δ የግል ንፅህናህን ጠብቅ
Δ ጥሩ የእንቅልፍ ጊዜ ይኑርህ
Δ በቀን ከሁለት እስከ ሶስት ብርጭቆ ውሃ ጠጣ
Δ ጤናማ የአተነፋፈስ ስርአት ይኑርህ
Δ መደበኛ ህክምና አድርግ
ክሊኒክ የምትሄደው ሲያምህ ብቻ ሳይሆን የደምግፊትህን ለማወቅ በደምህ ውስጥ ያለውን የስኴር መጠን ለማወቅ የአይንግፍት ኩላሉት ጤናማ መሆናቸውን ለማረጋገጥ መደበኛ ህክምና አድርግ
Δ በትክክል ተፀዳዳ
Δ በራስ የመተማመን ስሜት ትጋት አዲስ ነገርን የማወቅ ጉጉት ይኑርህ
Δ የእርጋታ መንፈስህን አዳብር
Δ የበሽታ መተላለፊያ መንገዶችን ተጠንቀቅ
Δ ስትቀመጥ ስትበላ ስትጠጣ ስትጓዝ በትክክለኛው መንገድ ይሁን
Δ ሂወትክን ከሌሎች ሰዎች ሂወት ጋር አታወዳድር
Δ አንተ ልትቆጣጠራቸውና ልትቀይራቸው በማትችላቸው ነገሮች ላይ አትጨነቅ አትጠበብ
Δ ፈገግተኛና ተጫዋች ሁን
Δ ቅናትን አስወግደህ መሆን በምትችልበት ነገር ላይ ስራ
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|